አቲቲ ዎረና
ድሮ ነው ገና ድሮ ከሃምሳና ከዚያ በላይ ዓመታት በፊት ያኔ አያቴ የእናቴ እናት ታደርገው የነበረዉ አሁን ዝት እያለኝ በዓእምሮየ መመላለስ ጀምሮአል ለምንድን ነው አሁን ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ትዝ ይለኝ የጀመረዉ መልስሁን አብረን እንፈልገዉ
እኔ ሳዉቅ አያቴ መአዛዉትነት ዕድሜ ክልል ዉስጥ እንደነበረች ፅ ይለኛል አያቴ ብዙ መናገር አትዎድም እናም ዝምተኝ ከሚባሉት ዉስጥ የምትመደብ ነበረች ለጆች ዎላልዳ ነበር እና ለልጆቿ እና ለልጅ ልጆቿ በመደገስ ነበር ጊዜዋን የምታሳልፈዉ እኔ የምኖረዉ ከአባቴ ጋር ትንሽ ራቅ ካለ ቦታ በመሆኑ ከአያቴ ጋር የምገናኘዉ አልፎ አልፎ በዓመት በዓል ቀናት እና በአጋጣሚ የጉብኝት ቀናት ነበር
ትዝ ዪለኛል አያቴ እንዴት በፍቀር ዓይን እንደምታኝ ያ ፍቅሯ ግን ያኔ ለእኔ ብዙም አይታየም ነበር እሷ ግን በልቸ የምጠግብ አይመስላት ከተኛሁ ደግሜ የምነሳ አይመስላት እንዲያው ምን አለፋችሁ ጻሳልኝ ነበር ዛሬ አፈሩን ያቅልልላትና፤
ዓመት በዓልማ ሲሆን ምኑ ይነሳል ሁሉም ዘመድ ከያለበት ይሰበሰባል የአያቴም ቤት በፍቅር ይሞላል ልጆቹ በአንድ በኩል አባቶች በሌላ እናቶች በአንዱ ሆነው ናፍቆታቸዉን በጨዋታ ሲዎጡ ይኑሮ ገጠመኞቻቸዉን በሃሳብ ሲለዋወጡ ያየ ፍቅር ግን ጥግ አለዉ ማለቱ አይቀርም
ዕጥብ ሳር ተጎዝጉዞና አዳራሹ ከአፍ እስከ ገደቡ ግጥም ብሎ የደሮ አይን ጠላ እየኮመኮሙ ከንፁህ አዕምሮ በመነጨ ጨዋታ እያዎኩ መውል ማደር ምንኛ የአዕምሮ ርካታ ይሰጣል በዓመትባል መሰባሰቡ በአያቴ ቤት ብቻ የሚከናዎን አይደለም ሁሉም ለአካ ለመጠን የደረሰ ልጅም ሆነ የልጅ ልጅ በዓመት አንድ ጊዜ መደገሱ አይቀርም.
የኔ ነገር የጊዜን ርዝመት መልካት የማይችለዉ ትዝታ ይዞኝ ነጎደና የተነሳሁበትን ረሳሁት
አቲቲ ዎረና አቲቲ ዎረና በሴት የተመሰለች አያቴ የማታያት የማትዳስሣት ሁሉም በዓለም ላይ ያለ ነገር ሁሉ ግን የሚከናዎነው በአቲቲ ወረናዋ መግነጢሳዊ ሃይል ሞሆኑን የምታምን እንደነበረ አቲቲዋን በዓመት አንድ ጊዜ ስታከብር ታደርገዉ የነበርዉ ሺር ጉድ ነዉ ዛሬ በዓዕምሮየ ድቅን እያለ ያስገረኝ እና አያቴና መሰሎቿ ይህችን አቲቲ ያክብሩ የነበርዉ ያዛሬን እዝነ ልቦናቸዉ ነግሮአቸዉ ነው ዎይስ
አንተው ናማ ናማ አንተዉ ናማ
አንተው ናማ ናማ አንተዉ ናማ
የበርሃዉ ንጉስ አንተዉ ናማማ
የጃርሶዉም ንጉስ ማን ይናገረዋል
የጫቃታን ንጉስ ማን ይናገረዋል
እጅ እግሩን ሰባብሮ ያነባርረዋል
እየለች ስታንጎራጉር ልክ እንደ ህልም ነዉ የአያቴ ድርጊት ትዝ እያለኝ የመጣዉ ታዲያ የዚህ በዓል እንበለዉ ዎይም ሌላ ስም ስጡት ዝግጅት ቀላል አልነበረም
የበዓሉ አከባበር የሚከናዎነዉ አዲሱ ዓመት አልፎ አሮጌዉ ዓሞት ሊገባ ሲል ነዉ ይመስለኛል መስከረም መጨረሻና ጳጉሜን ላይ
በዓሉ ከአምስት እስከ ሰባት ቀን ይዎስዳል ትዝ እንደሚለኝ ለዚህ ታዲያ አያቴ የምታደርገዉን ዝግጅት አትጠይቁኝ የኔ ትኩረት በነዚያ አምስት እና ሰባት ቀናት ላይ ብቻ በመሆኑ
አያቴ በነዚህ ቀናት ብቻ የሚለበስ በሌሎች ከናት ግን ከሳጥን የማይዎጣ ቀሚስ አላት ቀሚሡ ከእጅ ፈትል የተሰራ ሆኖ ቁመቱ በጣም ረጂም ነዉ ጥለቱ ከኋላ በኩል ብቻ ህኖ ሰፋ ያለ ጃኖ ነዉ ከታች ሰፊ ጃኖ ይኑረዉ እንጂ የአያቴ ቃሚስ ዙሪያዉን እንድ ቀይ ጥቁር እና ሌሎችም ቀለማት ከላይ እስከ ታች ዙሪያዉን አሉት ይህ ብቻ አይደለም የተለያዩ ቀለማት የሰካኩብት ጭሌ ከቀሚሱ አይለይም
ብሌ በኩል የበዓሉ ቀናት ከመድረሳቸዉ በፊት አያቴ ሥራ በጣም ይበዛባታል ስንዴ አጥባና አድርቃ ስትገረድፍ አያታለሁ ዎተት ተገፍቶ ቅቤዉ ሲዎጣ ከዚያ ከወጣዉ ቅቤ ዉስጥ ገምደል አድርጋ በቅጥል ጠቅለል አድርጋ ለብቻዉ ታስቀምጣለች ከአያቴ ቤት ከዓመት እስከ ዓመት ጠላ ከቤት አይጠፋም ያን ሰሞን ግን ስንዴ አዉጥታ አዲስ ብቅል ታበቅል ነበር ከትልቁ ቤት ባሻገር እንዲት ትንሽ እልፍኝ አለች እልፍኟ ለእንግዳ ማረፊአ እና ለመሳሰሉት ታገለግላለች ያን ሰሞም ታዲአ ፍንትዉ ብላ ነው የተለቀለቀችዉ የአያቴን የሳምንቱን ለየት ያለ እንቅስቃሴ የሚያይ ሁሉ መገረሙ አይቀርም።
የበዓሉ አከባበር ይቀጥላል.
Comments
Post a Comment