አቲቲ ዎረና
ድሮ ነው ገና ድሮ ከሃምሳና ከዚያ በላይ ዓመታት በፊት ያኔ አያቴ የእናቴ እናት ታደርገው የነበረዉ አሁን ዝት እያለኝ በዓእምሮየ መመላለስ ጀምሮአል ለምንድን ነው አሁን ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ትዝ ይለኝ የጀመረዉ መልስሁን አብረን እንፈልገዉ እኔ ሳዉቅ አያቴ መአዛዉትነት ዕድሜ ክልል ዉስጥ እንደነበረች ፅ ይለኛል አያቴ ብዙ መናገር አትዎድም እናም ዝምተኝ ከሚባሉት ዉስጥ የምትመደብ ነበረች ለጆች ዎላልዳ ነበር እና ለልጆቿ እና ለልጅ ልጆቿ በመደገስ ነበር ጊዜዋን የምታሳልፈዉ እኔ የምኖረዉ ከአባቴ ጋር ትንሽ ራቅ ካለ ቦታ በመሆኑ ከአያቴ ጋር የምገናኘዉ አልፎ አልፎ በዓመት በዓል ቀናት እና በአጋጣሚ የጉብኝት ቀናት ነበር ትዝ ዪለኛል አያቴ እንዴት በፍቀር ዓይን እንደምታኝ ያ ፍቅሯ ግን ያኔ ለእኔ ብዙም አይታየም ነበር እሷ ግን በልቸ የምጠግብ አይመስላት ከተኛሁ ደግሜ የምነሳ አይመስላት እንዲያው ምን አለፋችሁ ጻሳልኝ ነበር ዛሬ አፈሩን ያቅልልላትና፤ ዓመት በዓልማ ሲሆን ምኑ ይነሳል ሁሉም ዘመድ ከያለበት ይሰበሰባል የአያቴም ቤት በፍቅር ይሞላል ልጆቹ በአንድ በኩል አባቶች በሌላ እናቶች በአንዱ ሆነው ናፍቆታቸዉን በጨዋታ ሲዎጡ ይኑሮ ገጠመኞቻቸዉን በሃሳብ ሲለዋወጡ ያየ ፍቅር ግን ጥግ አለዉ ማለቱ አይቀርም ዕጥብ ሳር ተጎዝጉዞና አዳራሹ ከአፍ እስከ ገደቡ ግጥም ብሎ የደሮ አይን ጠላ እየኮመኮሙ ከንፁህ አዕምሮ በመነጨ ጨዋታ እያዎኩ መውል ማደር ምንኛ የአዕምሮ ርካታ ይሰጣል በዓመትባል መሰባሰቡ በአያቴ ቤት ብቻ የሚከናዎን አይደለም ሁሉም ለአካ ለመጠን የደረሰ ልጅም ሆነ የልጅ ልጅ በዓመት አንድ ጊዜ መደገሱ አይቀርም. የኔ ነገር የጊዜን ርዝመት መልካት የማይችለዉ ትዝታ ይዞኝ ነጎደና የተነሳሁበትን...